Fana: At a Speed of Life!

በአብየ የተሰማራው የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ በአሚት የገበያ ስፍራ በእሳት ቃጠሎ ጉዳት ለደረሰባቸው ነዋሪዎች የተለያዩ የምግብ አይነቶች ድጋፍ አደረገ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 2 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)በአብየ የተሰማራው የ23ኛ ሞተራይዝድ ሰላም አስከባሪ ሻለቃ በአሚት የገበያ ስፍራ በእሳት ቃጠሎ ጉዳት ለደረሰባቸው ነዋሪዎች የተለያዩ የምግብ አይነቶች ድጋፍ አድርጓል፡፡

የሻለቃው አዛዥ ኮሎኔል ሃሰን አብደላ ድጋፉን ባስረከቡበት ወቅት እንደተናገሩት ÷ ሻለቃው የቀጣናውን ሰላም ከማስፈን ባሻገር  በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ አደጋ ለችግር ለሚዳረጉ ወገኖች ፈጣን ምላሽ መስጠት ሌላው የሰራዊቱ ተልዕኮ መሆኑን ገልፀው  የዛሬው ድጋፍም የዚሁ ማሳያ ነው ብለዋል፡፡

አዛዡ አያይዘውም የእሳት ቃጠሎውን ተከትሎ ግጭቶችና ዝርፊያዎች እንዳይፈፀሙ የተጠናከረ ጥበቃ በማድረግ የአካባቢውን ሰላም የማረጋገጥ ሰራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

ዛሬ የተደረገው ድጋፍ የመጀመሪያ መሆኑን ጠቁመው ÷ በቀጣይ ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች አቅም በፈቀደ መጠን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ነን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

የጎሳ መሪዎቹና የሰላም ኮሚቴዎች በበኩላቸው ÷ ሰራዊቱ አደጋውን ለመቆጣጠር በተደረገው ጥረት በነበረው ተሳትፎ አመስግነው  ለተደረገላቸው ሰብዓዊ ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በዚህም 1ሺህ 274 ሊትር ጁስ ፣ 480 ኪ.ግ ሩዝ ፣ 104 ኪ.ግ ፓስታ ፣ 54 ኪ.ግ ቲማቲም ድልህ ፣ 35 ኪ.ግ ፉርኖ ዱቄት፣ 28 ሊትር ዘይት፣ 32 ኪ.ግ ጨው እና ሌሎች የምግብ አይነቶች ድጋፍ መደረጉ ከኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት ገጽ ያገኘኘው መረጃ ያመላክታል።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.