Fana: At a Speed of Life!

በየክልሉ የሚገኙ የተሀድሶ ህክምና መስጫ ማዕከላትን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 2 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በኢትዮጵያ የተሀድሶ ህክምናና የሰው ሰራሽ የአካልና የአካል ድጋፍ አገልግሎትን ማጠናከር እንደሚገባ ተገለጸ።

በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ ሥር የሚገኘውን የአዲስ አበባ የሰው ሰራሽ አካል እና የአካል ድጋፍ መስጫ ማዕከልን ከጎበኙ በኋላ የሰው ሰራሽ የአካልና የአካል ድጋፍ መስጫ ማዕከሉ የሚሰጠውን አገልግሎት ወደ የላቀ ደረጃ ለማሳደግና የተሀድሶ ህክምና አገልገሎት የልህቀት ማዕከል እንዲሆን አቅጣጫ መስጠታቸው ይታወሳል፡፡

ይህንን የማስፈጸም ሂደት የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ እና የመከላከያ ሚኒስትሩ ዶ/ር ቀነዓ ያደታ ይመሩታል።

የሰው ሰራሽ አካል እና የአካል ድጋፍ መስጫ ማዕከልና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ስር የሚተዳደረው የሚኪሊላንድ የተድሶ ህክምና አገልግሎት መስጫ ማዕከል ከጎበኙ በኋላ ሁለቱ ሚንስትሮች በጋራ ከጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት፣ ከብሄራዊ የተሀድሶ ህክምና ግብረ-ሀይል እና ከመከላከያ ለተወጣጡ የኮሚቴ አባላት አቅጣጫ ሰጥተዋል።

በሰጡት አቅጣጫ መሰረትም የአዲስ አበባ የሰው ሰራሽ የአካልና የአካል ድጋፍ አገልግሎት መስጫ ማዕከልን በማስፋፋት እና በማጠናከር ሁሉን አቀፍ የአካላዊ ተሃድሶ ህክምና፣ የአእምሮና የማህበራዊ ተሀድሶ አገልግሎቶች፣ የሰው ሰራሽ አካላዊ አጋዥ ቴክኖሎጂዎች የማምረት እንዲሁም ትምህርትና ስልጠናን አጠቃሎ የሚሰጥ ብሔራዊ አጠቃላይ ተሃድሶ ማዕከል ለማደራጀት የሚያስችል በጥናት ላይ የተደገፈ እቅድና መዋቅራዊ አደረጃጀት ተዘጋጅቶ በግብረ-ሀይሉ ለውይይት እንዲቀርብ ተደርጓል፡፡

በውይይቱም የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ፤ የመከላከያ ሚኒስትር ዶ/ር ቀነዓ ያደታ፤ የኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች ፌደሬሽን፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የስራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ፣ የእትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፓሬሽን እንዲሁም በአካል ታህድሶ ህክምና ድጋፍ ላይ የሚሰሩ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት ተሳታፊ ነበሩ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ የሚገኘው የሰው ሰራሽ የአካል እና የአካል ድጋፍ ህክምና መስጫ ማዕከል በአዲስ አደረጃጀት በአጭር ጊዜ ውስጥ በተጠናከረ መልኩ ወደ ስራ እንዲገባ አቅጣጫ የተቀመጠ ሲሆን በቀጣይም በየክልሉ የሚገኙ የተሀድሶ ህክምና መስጫ ማዕከላትን ማጠናከር እንደሚገባ ተገልጿል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.