Fana: At a Speed of Life!

አምባሳደር ፕሮፌሰር አድማሱ ፀጋዬ በኢንዶኔዢያ ከፊንላንድ አምባሳደር ጃሪ ሲንካሪ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 3 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢንዶኔዢያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፕሮፌሰር አድማሱ ፀጋዬ በኢንዶኔዢያ ከፊንላንድ አምባሳደር ጃሪ ሲንካሪ ጋር ተወያዩ፡፡

አምባሳደር ፕሮፌሰር አድማሱ ፀጋዬ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ስላለው ሁለንተናዊ ለውጥ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በትግራይ ክልል የተካሄደው የህግ የበላይነትን የማስከበር ስራ መጠናቀቁን፣ የመሰረተልማት መልሶ ግንባታ እና የሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉን አስረድተዋል፡፡

አምባሳደሩ ስለህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ የድርድር ሂደት እና ሱዳን ያለአግባ የኢትዮጵያን መሬት ስለመያዟ አብራርተዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.