Fana: At a Speed of Life!

የግብርና ሚኒስቴር አሲዳማ አፈርን በኖራ ውህድ ለማከም ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ነው

አዲስ አበባ፣ የካቲት 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የግብርና ሚኒስቴር አሲዳማ አፈርን በኖራ ውህድ ለማከም ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል፡፡

በኢትዮጲያ 36 ሚሊየን ሄክተር መሬት ሊታረስ የሚችል ሲሆን፤ 16 ሚሊየን ሄክታሩ ጥቅም ላይ እየዋለ ይገኛል ተብሏል፡፡

ከዚህ ውስጥ 43 በመቶ የሚሆነው አሲዳማ አፈር ሲሆን፤ ይህም 6 ሚሊየን ሄክታር የሚሆነውን መሬት ሲሸፍን፤ ከዚህ ውስጥም 3 ነጥብ 7 ሚሊየን ሄክታሩ የከፋ ጉዳት የደረሰበት ነው፡፡

አሲዳማ አፈር ያለበት መሬት ከ50 እስከ 100 በመቶ የምርት መቀነስ ሊያስከትል እንደሚችልም ተነግሯል፡፡

በኢትዮጵያ እስካሁን 89 ሺህ ሄክታር መሬት በውህድ ኖራ የታከመ ሲሆን፤ በታከመው መሬት ላይ በስንዴ ምርት 70 በመቶ ጭማሪ፣ በገብስ ምርት 100 በመቶ ጭማሪ፣ በበቆሎ 28 በመቶ የምርት ጭማሪ እንዲሁም በባቄላ 68 በመቶ የምርት ጭማሪ ታይቷል ነው የተባለው፡፡

ይህን ተከትሎም በመጭው የመኸር ወቅት 63 ሺህ ሄክታር መሬት አሲዳማ አፈር ለማከም የታቀደ ሲሆን፤ 1 ነጥብ 5 ሚሊየን ውህድ ኖራ እንደሚያስፈልግም ተነግሯል፡፡

ከ2014 እስከ 2017 ዓ.ም 500 ሺህ ሄክታር አሲዳማ አፈር ለማከም የታቀደ ሲሆን፤ በዚህም 62 ሚሊየን ኩንታል ተጨማሪ ምርት ሊገኝ ይችላልም ነው የተባለው፡፡

ይህም ከውጭ የሚገባውን የስንዴ ምርት ሊያስቀር እንደሚችል ታምኖበታል፡፡

በፀጋዬ ንጉስ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.