Fana: At a Speed of Life!

ወጣቶች አምራች ሃይል በመሆናቸው አዕምሯቸው ላይ ሊሰራ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣የካቲት 3፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ወጣቶች አምራች ሃይል በመሆናቸው አዕምሯቸው ላይ ሊሰራ ይገባል ተብሏል።

በጅማ ከተማ በወጣቶች ስነ-ልቦና እና ሠላም ላይ ያተኮረ የማህበረሰብ የምክክር መድረክ የተካሄደ ሲሆን፤ በከተማው ውስጥ እራሳቸውን የሚያጠፉ ወጣቶች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ በመምጣቱ ነው መድረኩ የተካሄደው።

በከተማው የሚስተዋለው እራስን የማጥፋት ሁኔታ ከወጣቱ አልፎ ቤተሰብ ላይ ከፍተኛ የስነ ልቦና ጫናና ስጋት እየፈጠረ መሆኑ ተመልክቷል።

በጅማ ዩኒቨርሲቲ የስነ ልቦና እና የአእምሮ ጤና ባለሙያ አቶ ጉተማ አህመድ በአብዛኛው እራስን የማጥፋት ችግር ከ15 እስከ 29 አመት ባሉ ወጣቶች ላይ እንደሚታይ ተናግረዋል።
በዚህ የእድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ወጣቶች ‘‘እኔ በማህረሰቡ ውስጥ ምንም ጥቅም የለኝም፤ ህብረተሰቡ እኔን አይፈልገኝም’’ የሚል ስሜት ሲሰማቸው እራሳቸውን ወደ ማጥፋት እንደሚያመሩ ባለሙያው ገልጸዋል።

በመሆኑም የእምነትተቋማት፣ የትምህርት ተቋማት፣ ማህበረሰቡ እንዲሁም ቤተሰቦች፤ ወጣቶች ተፈላጊ እንደሆኑና ወደፊትም ብሩህ ተስፋ እንደሚጠብቃቸው ሊያስገነዝቡ ይገባል ብለዋል።

ከዚህ በተጨማሪ እራሳቸውን ከሚያጠፉ ወጣቶች መካከል 90በመቶ የሚሆኑት የአዕምሮ ችግር አለባቸው ያሉት ባለሙያው፤ ቤተሰብ የልጆቹን ሁኔታ ሊከታተል እንደሚገባና የተለየ ነገር ሲያስተውልባቸው የባለሙያ ድጋፍ እንዲያገኙ ሊያደርጉ ይገባልም ነው ያሉት።

በሙክታር ጠሃ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.