Fana: At a Speed of Life!

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የተለያዩ ድጋፎችን አደረገ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ለትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የተሽከርካሪ፣ የቢሮ እና የፅህፈት መሳሪያዎች እንዲሁም የተለያዩ መሳሪያዎችን ድጋፍ አደረገ፡፡

የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም እና የገንዘብ ሚኒስቴር ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ተወያይተዋል፡፡

የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ያስሚን ወሀብሬቢ እና የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም የአፍሪካ ዳይሬክተር አሁና ኢዚኮኖዋ የተመራ ልዑክ በመቐለ ጉብኝት አድርጓል፡፡

ልዑኩ የአንድ ቀን ጉብኝት ያደረገ ሲሆን በትግራይ ክልል ስላለው ወቅታዊ ሁኔታ ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ እና ከሌሎች የጊዜያዊ አስተዳደሩ ባለስልጣናት ጋር ተወያይቷል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.