በትግራይ ሠላምና መረጋጋት እንዳይኖር የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ የዳያስፖራ አባላት ከድርጊታቸው ሊቆጠቡ ይገባል – ዶክተር ሙሉ ነጋ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 6፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በትግራይ ክልል ዘላቂ ሠላምና መረጋጋት እንዳይፈጠር የሚንቀሳቀሱ አንዳንድ የዳያስፖራ አባላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ዶክተር ሙሉ ነጋ አሳሰቡ፡፡
ዳያስፖራው መንግሥት በትግራይ ክልል እያደረገ ያለውን የሠብዓዊ ዕርዳታና መልሶ ግንባታ እንዲደግፍም ጠይቀዋል፡፡
አንዳንድ የዳያስፖራ አባላት በስሜታዊነት ክልሉን የጦርነት ቀጣና ከማስመስል እንዲወጡም ነው የጠየቁት።
ለራሳቸው የተደላደለ ኑሮ እየኖሩ ክልሉ ወደማያባራ ጦርነት እንዲገባ ለማድረግ መስራት ህሊና ቢስነት ነው ብለዋል፡፡
ይህ ተግባራቸው ወንጀል መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር ሙሉ የክልሉ ሕዝብ ራሱን ከእነዚህ አካላት እንዲጠብቅ አሳስበዋል፡፡
ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሕዝቡን ካለበት አስቸጋሪ ሁኔታ ለማውጣት እገዛ የሚያደርጉ የዳያስፖራ አባላትን እንደሚያስተናግድ ገልጸዋል፡፡
ክልሉን ከችግር ለማውጣት መፍትሄው መነጋገርና መወያየት መሆኑን የጠቆሙት ዶክተር ሙሉ፤ በስሜት ተነሳስቶ ሕዝብን ማደናገር ለማንም አይበጅም ብለዋል፡፡
ዳያስፖራው ሐሳቡን በተደራጀ መልኩ ወደ ክልሉ እንዲያቀርብም ነው ያመለከቱት፡፡
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በአብዛኞቹ ወረዳዎች መዋቅሩን ዘርግቷል ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!