Fana: At a Speed of Life!

አቶ ደመቀ መኮንን ከቱርኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር የሃገራቱን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ከቱርኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ ጋር የሃገራቱን ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ተወያዩ፡፡

በውይይቱ ወቅት በኢትዮ ሱዳን የድንበር ጉዳይ እንዲሁም የጋራ በሆኑ ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርገው መክረዋል፡፡

አቶ ደመቀ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጋር ያለውን የድንበር ውዝግብ በውይይት ለመፍታት ያላትን ፅኑ አቋም በተመለከተ ለቱርኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገለጻ አድርገዋል፡፡

ሁለቱ ሃገራት በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ግንኙነት በማድነቅም የሃገራቱን ትብብር እና ስትራቴጂካዊ አጋርነት ማሳደግ ይገባል ብለዋል፡፡

የቱርኩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሜቭሉት ካቩሶግሉ በበኩላቸው፥ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ለቱርክ ባለሃብቶች አንደኛዋ መዳረሻ መሆኗን አንስተዋል፡፡

በውይይታቸው ወቅት ሚኒስትሮቹ ሃገራቱ በተለያዩ ዘርፎች ያላቸውን ግንኙነት በማስታወስ፥ አጋርነታቸውን በተለያዩ ዘርፎች ማሳደግ እንደሚገባቸውም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡

ሚኒስትሮቹ ከውይይታቸው ባሻገር ኢትዮጵያ እና ቱርክ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት የጀመሩበትን 125ኛ አመት በጋራ ያከበሩ ሲሆን፥ በአንካራ አዲስ የተገነባው የኢትዮጵያ ኤምባሲም መርቀው ከፍተዋል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details?id=com.companyname.FanaAm በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.