Fana: At a Speed of Life!

የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታዋ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ዋና ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር ዲኤታ ያስሚን ወሀብረቢ ከአፍሪካ ልማት ባንክ ዋና ዳይሬክተር አሞስ ኪፕሮኖ ቼፕቶ ጋር ተወያዩ፡፡

በውይይታቸው ወቅት የአፍሪካ ልማት ባንክ በኢትዮጵያ የሚተገብራቸውን የልማት ፕሮጀክቶቸን እና ፕሮግራሞች በመደገፍ ሃገሪቱ ለነደፈችው የልማት ዕቅድ መሳካት ድጋፍ ከሚያደርጉ የልማት አጋሮች ባንኩ አንዱ በመሆኑ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በተጨማሪም የልማት ባንኩ በተለይም በመሰረተ ልማት ዝርጋታ፣ በትራንስፖርት፣ በኢነርጂ፣ በውሃና በንፅህና አጠባበቅ እና በግብርና የሚያደርገውን አስተዋፅኦ አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

ወሀብረቢ የአፍሪካ ልማት ባንክ ዋና ዳይሬክተር አሞስ ኪፕሮኖ ቼፕቶ በበኩላቸው፥ ባንኩ የኢትዮጵያን የሃገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራም ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት አረጋግጠዋል ፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details?id=com.companyname.FanaAm በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.