የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሩ ከዓለም ባንክ ተወካዮች ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሳሙኤል ኡርቃቶ ከዓለም ባንክ ተወካዮች ጋር ተወያዩ፡፡
በውይይቱ ወቅት በሚኒስቴሩ የከፍተኛ ትምህርት ማሻሻያ ተግባራት በተለይም በነገው እለት ይፋ በሚሆነው የሃገር በቀል የሶስተኛ ዲግሪ አፈጻጸም ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ የኤርትራ፣ የሱዳንና ደቡብ ሱዳን ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን በበኩላቸው፥ ለፕሮግራሙ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል፡፡
አያይዘውም የሴቶችን አካዳሚክ አሳታፊነትና ለትምህርቱ ዘርፍ ማሻሻያ ጠቃሚ የሆኑ ሌሎች የትኩረት መስኮች ላይም ትኩረት እንዲደረግ ማመላከታቸውን የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details?id=com.companyname.FanaAm በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!