መምህራንን ብቻ ማዕከል ያደረገ የአንበሳ አውቶብስ የመታወቂያ ማሻሻያ ሊደረግ ነው
አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከአንበሳ የከተማ አውቶብስ አግልግሎት ደርጅት እና ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ጋር ለመምህራን በሚቀርበዉ የአንበሳ አውቶብስ የትራንስፖርት አግልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ ውይይት አካሄዷል፡፡
በውይይቱ ለመምህራን እየቀረበ ያለዉ የአንበሳ አውቶብስ የትራንስፖርት አገልግሎት ትውልድን የመቅረጽ ስራዉን ለሚያከናውኑ መምህራን ሁሌም ቅድሚያ መስጠት ላይ ሊያተኩር እንደሚገባ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ገልጸዋል፡፡
ሀላፊዉ አክለዉም ሹፌሮች ፣ ትኬት ቆራጮች እና ተገልጋዩ ማህበረሰብ ይህንን በመረዳት የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር መምህራን ማህበር ፕሬዚዳንት አቶ ድንቃለም ቶሎሳ በመምህራን በኩል ከሚነሱ ጥያቄዎች መካከል አንዱና ዋነኛዉ የከተማ የአንበሳ አውቶብስ አጠቃቀም በመሆኑ ተደራሽነቱ እና አግልግሎት አስጣጡ የመምህራንን ጥያቄ በሚፈታ መልኩ መሆን አለበት ብለዋል፡፡
የከተማ አውቶብስ አግልግሎት ደርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ ገበየሁ ዋቄ ድርጅቱ የሚያቀርበዉን የትራንስፖርት አገልግሎት ቅድሚያ ለመምህራን በመስጠት እንደሚሰራ እና ለተቋሙ ሰራተኞችም በዚህ ልክ ግንዛቤ የመስጠት ስራ ይከናወናል ብለዋል፡፡
በውይይቱ መምህራንን ብቻ ማዕከል ያደረገ የአንበሳ አውቶብስ የመታወቂያ ማሻሻያ እንደሚደረግ ከመግባባት ላይ መደረሱን የከተማ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ከአዲስ አበባ ከተማ ትምህርት ቢሮ መረጃ ማግኘቱን አመልክቷል።
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ የመንግስት ትምህርት ቤቶች ውስጥ በማስተማር ላይ ላሉ መምህራን ነጻ የአንበሳ አውቶብስ የትራንስፖርት አገልግሎት በከተማ አስተዳደሩ በመቅረብ ላይ መሆኑ የሚታወስ ነዉ፡፡
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤
ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ
ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ
ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን
የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት መተግበሪያን https://play.google.com/store/apps/details… በስልክዎ በመጫን ቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት፣ ኤፍኤም 98.1 እና ብሄራዊ ሬዲዮን ይከታተሉ፡፡ ቪዲዮዎችንም ይመልከቱ፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!