Fana: At a Speed of Life!

ም/ጠ ሚኒስትርና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ ከዛሬ ጀምሮ በህንድ ጉብኝት ያደርጋሉ

 

አዲስ አበባ፣ የካቲት 9፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከዛሬ ጀምሮ በህንድ ጉብኝት ያደርጋሉ።

አቶ ደመቀ እስከ መጪው አርብ በህንድ በሚኖራቸው ቆይታ በተለያዩ ስነ ስርዓቶች ላይ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።

በዚህም በህንድ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያስገነባውን ህንፃ እና የዲፕላማቶች መኖሪያ ከህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጀሽንከር ጋር በመሆን በመጪው ሀሙስ ይመርቃሉ ተብሏል።

በተመሳሳይ አቶ ደመቀ ከህንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሱብራህማንያም ጀሽንከር ጋር በኢትዮጵያ እና ህንድ የሁለትዮሽ ግንኙነት ዙሪያ እንደሚወያዩ ነው የተነገረው።

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

የፋና ድረ ገጽ https://www.fanabc.com/ ይጎብኙ፤

ተንቀሳቃሽ ምስሎችን ለማግኘት የፋና ቴሌቪዥን የዩቲዩብ ቻናል https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ሰብስክራይብ ያድርጉ

ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት ትክክለኛውን የፋና ቴሌግራም ቻናል https://t.me/fanatelevision ይቀላቀሉ

ከዚህ በተጨማሪም በትዊተር ገጻችን https://twitter.com/fanatelevision ይወዳጁን

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.