በኮንስትራክሽን ዘርፍ የተሰማሩ ሁለት ኮርፖሬሽኖች ከታክስ በፊት ብር 257 ሚሊየን አተረፉ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመንግሥት ልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ኤጀንሲ ሥር ከሚገኙ 21 የልማት ድርጅቶች መካከል በኮንስትራክሽ ዘርፍ የተሰማሩት ሁለት ድርጅቶች 257 ሚሊየን ብር አተረፉ።
የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪው መንፈቅ 300 ሚሊየን ብር ትርፍ ከታክስ በፊት ለማግኘት አቅደው257 ሚሊየን ብር ማግኘታቸውን የኤጀንሲው የህዝብ ግንኙነት ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዳፍራሽ አሰፋ አስታውቀዋል፡፡
ትርፉ ኮርፖሬሽኖቹ በኮንስትራክሽን፣ በዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች በግማሽ በጀት ዓመቱ 2 ነጥብ 4 ቢሊየን ብር ለማግኘት አቅደው 1 ነጥብ 9 ቢሊየን ብር በማግኘት የዕቅዳቸውን 78 በመቶ ማከናወን በመቻላቸው የተገኘ ነው ተብሏል፡፡
ከሀገር ውስጥ በተጨማሪ በተለይም በአፍሪካ ሀሃገራት በኮንስትራክሽን ገበያ ገብተው ለመሥራትና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪ ሆኖ ለመገኘት ኮርፖሬሽኖቹ ባደረጉት ጥረት የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዲዛይንና ሱፐርቪዥን ሥራዎች ኮርፖሬሽን በታንዛኒያ ፣ ጅቡቲና ናይጄሪያ ገብቶ እየሠራ መሆኑም ተገልጿል።
የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ሥራዎች ኮርፖሬሽን ደግሞ ጅቡቲ ሥራ ማግኘቱም ነው የተገለጸው።
ኤጀንሲው ኦፕሬሽንን፣ ፋይናንስን እና ፕሮጀክትን በተመለከተ በስድስት ወሩ የታቀዱ ግቦች አፈጻጸም እና በቀጣይ ትኩረት አቅጣጫዎች ላይ ትኩረት አድርጎ ግምገማ ማድረጉን የኤጀንሲው መረጃ ያመላክታል።
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፦ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ዩቲዩብ ቻናል፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!