Fana: At a Speed of Life!

በአዲስ አበባ 10 ሺህ 500 የላዳ ታክሲዎች በአዳዲስ ታክሲዎች ሊተኩ ነው

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 10 ሺህ 500 ሰማያዊ በነጭ የላዳ ታክሲዎችን በአዳዲስ ታክሲዎች ለመተካት ዝግጅት ማጠናቀቁን የአዲስአበባ ትራንስፖርት ባለስልጣን አስታወቀ፡፡

ከሃምሳ ዓመታት በላይ አገልግሎት የሰጡትን እነዚህን ተሽከርካሪዎች በዘመናዊ ታክሲዎች መተካት የሚያስችል የስምምነት ፊርማ ስነስርዓት ተካሄዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ስጦታው አካል ላዳ ታክሲዎች ከ10 ሺህ በላይ ቤተሰቦችን እንደሚያስተዳድሩ ገልጸው ታክሲዎቹ የበርካታ አዲስ አበባውያን ባለውለታ ናቸው ብለዋል፡፡

አሁን ላይ የከተማዋን እድገት የሚመጥን የትራንስፖርት አገልግሎት ማቅረብ አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱንም ነው የተናገሩት፡፡

ከዚህ ባለፈም የታክሲዎቹ ዕድሜና ይዞታ ዘመኑን የማይመጥን በመሆኑ ተሽከርካሪዎቹን በአዳዲስ መተካት ማስፈለጉን አስረድተዋል፡፡

ታክሲዎቹን በአዳዲስ ለመተካት ከ6 ቢሊየን ብር በላይ ከንግድ ባንክ ብድር ተመቻችቷል፡፡

አዳዲሶቹ ታክሲዎች በሚቀጥሉት አራት ወራት ወደስራ ይገባሉ ተብሏል፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፦ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ዩቲዩብ ቻናል፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.