በለውጡ ማግስት ከተሞች ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸዋል – ኢንጂነር አይሻ መሀመድ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሴክተር የ2013 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ግማሽ አመት የዕቅድ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ በሐረር ከተማ መካሄድ ጀምሯል።
የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ሚኒስትር ኢንጂነር አይሻ መሀመድ በመድረኩ እንደተናገሩት በለውጡ ማግስት ከተሞች ልዩ ትኩረት ተሰጥቷቸዋል ብለዋል፡፡
በዚህም ከተሞች ለነዋሪዎቸቸው ምቹና በአገልግሎት አሠጣጣቸውም ቀልጣፋ ለማድረግ ስራዎች እየተሠሩ እንዳለ ጠቁመዋል።
ኢትዮጵያ የያዘችውን የብልፅግና ጉዞ ለመሳካት የባለድርሻ አካላት ትብብር አስፈላጊ መሆኑን ሚኒስትሯ አስታውቀዋል።
የሐረሪ ክልል ርዕሰመስተዳድር ኦድሪን በድሪ በበኩላቸው ከተሞች የሚገባቸውን ትኩረት ሳያገኙ በመቆየታቸው ነዋሪው ተጠቃሚ ሳይሆን ቀርቷል ነው ያሉት፡፡
በከተሞች የዜጎች ቻርተርና የማዘጋጃ ቤቶች አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሳለጥ የከንቲባዎች ፎረምን በማዋቀር የልምድ ልውውጥ በማድረግ የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩት ዕውቅና እንዲሠጥ መደረጉ በመድረኩ ተነግሯል፡፡
የመሬት አቅርቦትና ፋይናንስ የዘርፉ የስድስት ወራት ተግዳሮቶች መሆናቸውንም በመድረኩ ላይ ተጠቁሟል።
ዛሬ መካሄድ የጀመረው መድረክ እስከ ነገ የሚቀጥል ይሆናል፡፡
በእዮናዳብ አንዱዓለም
ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፦ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ዩቲዩብ ቻናል፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!