Fana: At a Speed of Life!

20 ሺህ ሜትሪክ ቶን የሚሆን ስንዴ ለትግራይ ክልል ተጓጉዟል -የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን

ኮሚሽን አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የብሔራዊ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ከአለም የምግብ ፕሮግራም ጋር በመቀናጀት እየሰራ እንዳለ አስታውቋል፡፡
የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደበበ ዘውዴ ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት እንደገለፁ 20 ሺህ ሜትሪክ ቶን ወይም 200 ሺህ ኩንታል ስንዴ ለትግራይ ክልል ተጓጉዟል፡፡
ግዢውን ለማከናወን በጀት የመደበው የኢትዮጵያ መንግስት ሲሆን የአለም የምግብ ፕሮግራም ግዢውን በማካሄድ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት እርዳታው ትግራይ ክልል መቐሌ ማዕከላዊ መጋዘን እንዲደርስ አድርጓል ብለዋል፡፡
በትግራይ ድጋፍ ለሚሹ ወገኖች ድጋፍ የማቅረብ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝም አቶ ደበበ ገልፀዋል፡፡
እስካሁን ድጋፉ ከሚያስፈልጋቸው ከ2 ሚሊየን በላይ ለሆኑት ድጋፍ ሲቀርብ ቀሪዎቹን ለማድረስ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በአዲ ሃሩሽ፣ ማይ አይኒ፣ መቐለ እና ሽሬ አልሚ ምግቦች እየደረሱ እንዳለም ኃላፊው ነግረውናል፡፡
በአጠቃላይ 300 ሺህ ሜትሪክ ቶን ስንዴ የመግዛት ዕቅድ ተይዞ እየተሰራ እንደሚገኝ የገለፁ ሲሆን በእቅድ ከያዘው የ200 ሺህ ሜትሪክ ቶን ስንዴ ግዢ መፈፀሙን ነው የነገሩን፡፡

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፦ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ዩቲዩብ ቻናል፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.