Fana: At a Speed of Life!

የአራት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የጊዜ ቀጠሮ ምርመራ ተቋረጠ

የአራት ከፍተኛ የጦር መኮንኖች የጊዜ ቀጠሮ ምርመራ ተቋረጠ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ምርመራ ቢሮ ህገ መንግስቱን በመናድ፣ ሚኒሻ በማሰልጠን እና ሚኒሻዎችን በማደራጀት በህወሓት ተገደን ገብተን ብለው ከዚህ በፊት በነበረ ቀጠሮ ለችሎት የገለጹት አራት መኮንኖች የጊዜ ቀጠሮ ምርመራ ተቋረጠ፡፡

የጦር መኮንኖቹ ጊዜ ቀጠሮ ይቋረጥ እንጅ ነጻ ተጠርጣሪዎቹ ናቸው አለመባሉን የፌደራል ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ከእስር ያልተፈቱ ሲሆን ነገርግን በፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የምርመራ ቡድን እየተከናወነ የሚገኘው የጊዜ ቀጠሮ መቋረጡን ያገኘው መረጃ  ያመላክታል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በትግራይ ክልል በአክሱም ከተደበቁበት ምሽግ በመውጣት በቤተሰባቸው አማካኝነት እጃቸውን ለመከላከያ መስጠታቸውን ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት መግለጻቸውም ይታወሳል፡፡

በዚህም የጊዜ ቀጠሮ ምርመራቸው እንዲቋረጥ የተደረጉት የጦር መኮንኖች

  1. ሜጀር ጀኔራል መሀመድ ኢሻ ዘይኑ ትኩእ
  2. ብርጋዴር ጀኔራል ሙሉጌታ በርሄ ይልማ
  3. ኮሎኔል ገብረእግዚአብሔር ገብረሚካኤል
  4. ኮሎኔል ገብረዋህድ ኃይሉ መሸሻ ናቸው፡፡

 

በታሪክ አዱኛ

ከፌስቡክ ገፃችን በተጨማሪ ወቅታዊ፦ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ዩቲዩብ ቻናል፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.