Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ሱዳን የውስጥ ደህንነት ጉዳዮች ልዑክ በኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ጉብኝት አደረገ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ሱዳን የውስጥ ደህንነት ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል አኮል ኩር የተመራ የደቡብ ሱዳን የልዑካን ቡድን ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ አመራሮች ጋር ተወያዩ፡፡

ውይይቱ በዋናነት ሁለቱ ሃገራት በኢንፎርሜሽንና በይነ መረብ ደህንነት ዙሪያ በጋራ ለመስራት በሚያስችላቸው ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ ነበር፡፡
ደቡብ ሱዳን ነጻነቷን ስታገኝ የኢትዮጵያ ሚና ከፍተኛ እንደነበር ያነሱት የደቡብ ሱዳን የውስጥ ደህንነት ጉዳዮች ዋና ዳይሬክተር ጄኔራል አኮል ኩር፥ አሁንም ደቡብ ሱዳን የተጠናከረ የበይነ መረብ ደህንነት ተቋም እንዲኖራት በማድረግ ረገድ የኢትዮጵያ ሚና ከፍተኛ እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡

የኢመደኤ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ሹመቴ ግዛው በበኩላቸው የደቡብ ሱዳንን የኢንፎርሜሽንና በይነ መረብ ደህንነት በማጠናከር ረገድ በዋናነት በሠው ሃይል ግንባታ፣ በቴክኖሎጂ ልማት እና በአሰራር ሥርአት ዝርጋታ ዙሪያ በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን ገልጸዋል፡፡

ሃገራዊም ይሁን ቀጠናዊ የኢንፎርሜሽንና በይነ መረብ ደህንነትን ለማረገጋጥ ሃገራት በጋራና በቅንጅት መስራት ይጠበቅባቸዋል መባሉን የኤጀንሲው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-  https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.