በቢሾፍቱ ከተማ የኢዜማ አባል ከነበሩት ግለሰብ ግድያ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ሰዎች ላይ ምርመራ እየተደረገ ነው – ፖሊስ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 10 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቢሾፍቱ ከተማ የኢዜማ አባል ከነበሩት አቶ ግርማ ሞገስ ግድያ ጋር በተያያዘ የተጠረጠሩ ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለው ምርመራ እየተደረገባቸው መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ከቢሾፍቱ ፖሊስ መምሪያ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመላክተው በአሁኑ ወቅት ተጨማሪ ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር የማዋል ስራ እየተሰራ ነው፡፡
ፖሊስ መምሪያው በተጠርጣሪዎች ላይ የሰውና የሰነድ ማስረጃዎችን በማጠናከር የምርመራ ስራውን እያከናወነ መሆኑንም አስታውቋል፡፡
አቶ ግርማ ሞገስ ባለፈው እሁድ ምሽት ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች በጥይት መገደላቸውን ፖሊስ መግለጹ ይታወሳል፡፡
በታሪክ አዱኛ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!