Fana: At a Speed of Life!

5 ከፍተኛ መኮንኖች ወደ መከላከያ ጦር ፍርድ ቤት ተዛወሩ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 11፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የመከላከያ ሬዲዮ ግንኙነትን በማቋረጥ በሰሜን ዕዝ ጦር ላይ ጥቃት እንዲደርስ አድርገዋል የተባሉት 5 ከፍተኛ መኮንኖች ወደ መከላከያ ጦር ፍርድ ቤት ተዛወሩ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ብርጋዴር ጀኔራል ገብረ ህይወት ሲኖሲዮስ፣ ብርጋዴር ጄኔራል ኢንሶ ኢጃጆ፣ ብርጋዴር ጄኔራል ፍስሃ ገብረስላሴ፣ ኮሎኔል ደሳለኝ አበበ እና ኮሎኔል እያሱ ነጋሽ ናቸው፡፡

ከዚህ ቀደም በፌደራል ፖሊስ ሲከናወን የነበረው ምርመራ ተቋርጦ ወደ መከላከያ ጦር ፍርድ ቤት መዛወራቸውን ፖሊስ ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት ዛሬ ገልጿል፡፡

ነገር ግን ሜጀር ጄኔራል ገብረመድህን ፍቃዴ (ወዲ ነጮ) እና ሜጀር ጄኔራል ይርዳው ገብረ መድህን ፍርድቤት ቀርበው በፖሊስ የመጨረሻ 10 ቀናት ምርመራ ማጠናቀቂያ ጊዜ ተጠይቆባቸዋል፡፡

ጠበቆቻቸውም እስካሁን የታሰሩት በቂ ነው ሲሉ መቃወሚያ አሰምተዋል፡፡

ከመርማሪ ጋር አብሮ በችሎት የቀረበው ዐቃቤ ህግ ምርመራው ከባድና ውስብስብ እንደነበር በማብራራት ሰፊ ማስረጃ እንደቀረበባችው ገልጿል፡፡

ፍርድቤቱም ለመጨረሻ ጊዜ 10 ቀናትን ፈቅዶላቸዋል፡፡

በታሪክ አዱኛ

ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.