Fana: At a Speed of Life!

የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ተካሄደ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 11 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ ብልፅግና ፓርቲ የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ዛሬ ተከናውኗል፡፡

በምርጫ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በአዲስ አበባ ያለውን የኑሮ ውድነትና የመኖሪያ ቤት ችግር ለመፍታት የአምስት አመት እቅድ በመንደፍ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ብልፅግና ፓርቲ ሁሉንም ዜጋ በእኩል የሚያይ እና ለጋራ ብልፅግና የሚተጋ መሆኑንም ተናግረዋል።

ፓርቲው ህብረብሄራዊነት ለሀገራዊ አንድነት መፍትሄ ለማድረግ እንደሚሰራም ነው የተናገሩት።

በተለይም ብልፅግና ኢትዮጵያ በችግር ውስጥ በነበረችበት ወቅት የተፈጠረ የለውጥ ኃይል መሆኑን በማንሳት በቀጣይም ለህዝቦች ብልፅግና ይሰራል ብለዋል ምክትል ከንቲባዋ።

የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መለሰ ዓለሙ በበኩላቸው ብልጽግና እና ለውጥ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽ ናቸው ብለዋል፡፡

አቶ መለስ ብልጽግና በለውጡ ሂደት የውስጥ ስበትና የውጭ ግፊት ተቋቁሞ በተስፋና ስኬት ታጅቦ ከተወለደ አንድ አመት ያስቆጠረ ዘመን ተሻጋሪ ሃሳብ ይዞ የመጣ የለውጡ ፍሬ መሆኑንም ጠቅሰዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.