Fana: At a Speed of Life!

84ኛው የሰማዕታት ቀን ታስቦ ዋለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 12፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በ84ኛው የየካቲት 12 ሰማዕታት መታሰቢያ ቀን ላይ በስድስት ኪሎ የመታሰቢያ ሀውልት በመገኘት የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል።

በተጨማሪም የአባት አርበኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን የአበባ ጉንጉን ያስቀመጡ ሲሆን በሰማዕታት መታሰቢያ ቀን ላይ አርበኞች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል ።

በበአሉ የዛሬ 84 አመት ጣሊያን ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት የካቲት 12 ቀን 1929 ዓ.ም 30 ሺህ የአዲስ አበባ ነዋሪዎች በግፍ የተጨፈጨፉበት ታሪክ ይታሰባል፡፡

በዕለቱ አብርሃ ደቦጭና ሞገስ አስገዶም በጦር አዛዡ ሩዶልፎ ግራዚያኒ ላይ ቦንብ ወርውረው ጉዳት በማድረሳቸው የጣሊያን ጦር በአዲስ አበባ ነዋሪዎች ላይ ጭፍጨፋ ፈፅሟል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-  https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.