Fana: At a Speed of Life!

የዋግኽምራ ዞን ነዋሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ እና ሀገራዊ ለወጡን በመደገፍ ሰልፍ አካሄዱ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰቆጣ ከተማና አካባቢው ነዋሪዎች ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድና በእርሳቸው አመራርነት የመጣውን ሀገራዊ ለውጥ በመደገፍ ሰላማዊ ሰልፍ አካሄዱ፡፡

ነዋሪዎቹ ለውጡን እንደግፋለን፣ ወደፊትም እንራመዳለን፣ ጁንታው በቆፈረው ጉድጓድ ራሱ ተቀብሯል፣ ኢትዮጵያዊነት ከሁሉም በላይ ነው፣ ፅንፈኝነት ይውደም ኢትዮጵያዊነት ይለምልም የሚሉት መፈክሮችን አሰምተዋል።

ሰልፈኞቹ የተጓዝነው መንገድ አጭር፣ የሚቀረው መንገድ ረዥም በመሆኑ ከመሪዎቻችን ጋር እንሻገራለን፤ የዩኒቨርሲት ጥያቄያችን በብልፅግና እውን ይሆናል የሚሉና መሰል መፈክሮችንም አንግበዋል።

የድጋፍ ሰልፉ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በሳል አመራር በሀገሪቱ የመጣውን ለውጥ በመደገፍ እውቅና መስጠትን አላማ ያደረገ ነው።

በተጨማሪም ሰልፉ በህግ ማስከበር ዘመቻው የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የሀገር መከላከያ ሰራዊት፡ ለአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ አባላት እውቅና የሚሰጥ መሆኑም ታውቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡-  https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.