በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደር ከአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጋር ተወያዩ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 12 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኢትዮጵያ የስዊድን አምባሳደር ሀንስ ሄንሪክ ልንድኩዊስት ከአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር ጋር ተወያይተዋል፡፡
በውይይታቸው ወቅትም በክልሉ የልማት እንቅስቃሴ እና ሰብአዊ ድጋፍ ዙሪያ መክረዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም የስዊድን መንግስት በአማራ ክልል በዩኒሴፍ አማካኝነት ድጋፍ በሚያደርግባቸው ቦታዎች ጉብኝት አድርገዋል፡፡
በጉብኝታቸው ወቅትም በልማታዊ ሴፍቲኔት ዘርፍ በሚደረገው ድጋፍ የሙከራ ፕሮጀክት በሚተገበርበት ወረዳ በመገኘት ከሚመለከታቸው የስራ ሃላፊዎች ጋርም ውይይት አድርገዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!