ኢዜማ የምርጫ መወዳደሪያ ምልክቱን አስተዋወቀ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ /ኢዜማ/ ፓርቲ የምርጫ መወዳደሪያ ምልክትና መሪ ቃል አስተዋውቋል።
ፓርቲው አንደኛ መደበኛ ስብሳባውን ማካሄድ ሲጀምር የመወዳደሪያ ምልክቱ ‘ሚዛን’ መሪ ቃሉም ‘ንቁ ዜጋ ምቹ አገር’ መሆኑን ለአባላቱ አስተዋውቋል።
የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ ፓርቲያቸው የተሻለ ተፎካካሪ ሆኖ ለመውጣት ዝግጅቱን እያጠናቀቀ መሆኑን ጠቁመዋል።
ምርጫ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች የምረጡኝ ቅስቀሳ እየተካሄደ መሆኑንም አክለዋል።
በስብሰባው የመወዳደሪያ ምልክትና መሪቃል ከማስተዋወቅ ባለፈ የፓርቲውን ፖሊሲ ይፀድቃል፤ ለምርጫ ዝግጅት የተሰሩ ስራዎችም ለዕጩ አባላት ይፋ ይደረጋሉ ብለዋል።
የፓርቲው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ናትናኤል ፈለቀ መጪውን አገራዊ ምርጫ ስኬታማ ለማድረግ የአገሪቷን ሠላምና ደህንነት ማስከበር ላይ ትኩረት ማድረግ እንደሚገባ ገልፀዋል።
ምርጫው ዴሞክራሲያዊና ሠላማዊ እንዲሆን መንግስት ለሁሉም ተፎካካሪ ፓርቲዎች ምቹ ሁኔታ ሊፈጥር እንደሚገባም አመልክተዋል።
በፓርቲው አንደኛ መደበኛ ስብሰባ ከሁሉም የአገሪቷ አካባቢዎች የተወከሉ ዕጩ ተወዳዳሪዎችና አመራሮቹ መታደማቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!