በተከለሰዉ የስፖርት ፖሊሲ ዙሪያ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በስፖርት አለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ለማሳደግ በተከለሰዉ የስፖርት ፖሊሲ ዙሪያ ከዘርፉ ባለድርሻ አካላት ጋር ዉይይት ተካሄደ፡፡
የባህልና ቱሪዝም ሚኒሰቴር ከወጣቶች ስፖርት አካዳሚ፣ ከጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚና ከወጣቶችና ስፖርት ኮሚሽን ጋር በጋራ በመሆን ባዘጋጁት ረቂቅ ላይ የስፖርት ፖሊሲ ክለሳ ዙሪያ ዉይይት ተካሂዷል፡፡
በዉይይቱም ከባህልና ቱሪዝም ሚኒሰቴር፣ ከጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ፣ ወጣቶች ስፖርት ኮሚሽንና ከወጣቶች ሰፖርት አካዳሚ ተወካዮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተካፍለዋል።
በውይይቱም ፖሊሲው የስፖርት አደረጃጀትና አሰራር፣ የስፖርት መሰረተ ልማት፣ የስፖርት ትጥቅና ቁሳቁሶች እንዲሁም ስፖርት ለሁሉም በሚሉ ርዕሰጉዳዮች ዙሪያ ተመክሯል፡፡
በተጨማሪም የባህል ስፖርት ልማት፣ የላቁ ስፖርተኞች ልማት፣ የስፖርት ዉድድር አስተዳደርና ልማት፣ የስፖርት ህክምናና ማገገሚያ፣ የስፖርት ፋይናንስና የስፖርት ንግድና ስፖርት ለሃገራዊ እድገትና ብልጽግና ማደግ ላይ ትኩረት ያደረጉ ሀሳቦች ላይ ውይይት ተካሂዷል፡፡
ፖሊሲዉ አለም አቀፍ ተወዳዳሪነትን ለማምጣት፣ የስፖርት መሰረታዊ ልማትን ተደራሽ ለማድረግ፣ የህብረተሰብ የስፖርት ተሳትፎ እንዲዳብር፣ የላቁ ስፖርተኞችን ለማፍራት፣ ስፖርትን ዘመናዊ ተቋም ለማድረግና ስፖርትን ለሀገር እድገት ለመጠቀም ከፍተገኛ ሚና እንዳለው በውይይቱ ተገልፃል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!