በባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር የወጣቶች የሥራ ዕድል ፈጠራ እንዳሳሰባቸው የከተማዋ የምክር ቤት አባላት ተናገሩ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በባሕር ዳር ከተማ የሥራ ዕድል ፈጠራን በአብቁተ የተቀማጭ ገንዘብ ማሳደግ እንደሚገባ የከተማዋ የሥራ ዕድል ፈጠራ አፈፃጸም በምክር ቤት ደረጃ በተገመገመበት ወቅት ተገልጿል፡፡
የሥራ አጥነት ሁኔታ አሳሳቢ መሆኑንና የሥራ ዕድል ፈጠራ አፈፃጸሙ ውስንነት እንዳለበት የከተማዋ የምክር ቤት አባላት አንስተዋል፡፡
ባለፉት ስድስት ወራት ለመተግበር ከታሰበው የሥራ ዕድል ፈጠራ ዕቅድ አፈፃጸሙ 37 ነጥብ 3 በመቶ ብቻ መሆኑንም የምክር ቤቱ አባላት ተናግረዋል፡፡
በሥራ ዕድል ፈጠራ 80 በመቶው ቋሚ እንዲሆን ቢጠበቅም በስድስት ወራቱ ከተፈጠረላቸው መካከል 46 ነጥብ 5 በመቶው የሚሆኑት ጊዜያዊ የሥራ ዕድል የተፈጠረላቸው ናቸው፡፡
የተዘዋዋሪ ብድር አሰጣጥ መመሪያ አስቸጋሪ መሆን፣ የመሬት አቅርቦትና አዳዲስ ሼድ አለመገንባት በወጣቶች የሥራ እድል ፈጠራ የተስተዋሉ ችግሮች መሆናቸውን አንስተዋል።
የተዘዋዋሪ ፈንድ የብርድ አመላለስ መመሪያ አበዳሪ ተቋም ያስቀመጠው መሥፈርት በመሆኑ ከተወሰደ ብድር መካከል 97 በመቶ ያህሉ ካልተመለሰ መበደር እንደማይቻል በውይይቱ ተነስቷል፡፡
በዚሁ መሰረትም 13 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ገደማ ያልተመለሰ እዳ መኖሩ ነው የተገለፀው፡፡
መደበኛ የብድር አገልግሎት ግን መቀጠሉን በመግለጽ የመሬት አቅርቦት እንዲኖር እየተሠራ መሆኑን የዘገበው አብመድ ነው፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!