የኦሮሚያ ክልል ወደ ኢንቨስትመንት ለተሸጋገሩ 6 ሺህ አርሶና አርብቶ አደሮች ስልጠና መስጠት ጀመረ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 13፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የኦሮሚያ ክልል ወደ ኢንቨስትመንት ለተሸጋገሩ 6 ሺህ አርሶና አርብቶ አደሮች ስልጠና መስጠት ጀመረ፡፡
500 የሚሆኑ የጅማ፣ ቡኖ በደሌ እና የኢሉ አባራ ዞን አርሶ እና አርብቶ አደሮች በጅማ ከተማ ስልጠናውን መከታተል ጀምረዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙት በክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የኦሮሚያ የግብርናና ገጠር ልማት ክላስተር አስተባባሪ ዶክተር ግርማ አመንቴ ስልጠናው በየክላስተሩ በክልሉ እንደሚሰጥ ተናግረዋል፡፡
ስልጠናው ስራ ፈጠራ፣ የገንዘብ አያያዝ እና ችግር ሲያጋጥም የመፍቻ ብልሀቶች ላይ ያተኮረ ነው ብለዋል፡፡
አርሶና አርብቶ አደሮቹ 27 ቢሊየን ብር በላይ የሚያወጣ የኢንቨስትመንት ስራ ላይ ሊሰማሩ በዝግጅት ላይ ናቸው ብለዋል ዶክተር ግርማ አመንቴ፡፡
በዚህም በመጀመሪያ ዙር ቁጠባ 3.5 ቢሊየን ብር ባንክ የሚያስቀምጡ ሲሆን፣ 30 ቢሊየን ብሩን ደግሞ ከኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ እና ከአዋሽ ባንክ በብድር የሚያገኙ ይሆና ነው የተባለው፡፡
ወደስራ በሚገቡ የኢንቨስትመንት አማራጮችም ለ133 ሺህ ዜጎች የስራ ዕድል ይፈጠራል ተብሎ ይጠበቃል፡፡
በብዙአለም ቤኛ
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!