በመዲናዋ የሚታየውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመፍታት ከመንግሥት በተጨማሪ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎውን ሊያጠናክር ይገባል – ወ/ሮ አዳነች አቤቤ
አዲስ አበባ፣ የካቲት 14፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የሚታየውን የመኖሪያ ቤት እጥረት ለመፍታት ከመንግሥት በተጨማሪ የግሉ ዘርፍ ተሳትፎውን ይበልጥ ሊያጠናክር ይገባል ሲሉ ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናገሩ።
ምክትል ከንቲባዋ ይህንን ያሉት ዛሬ በትራኮን ትሬዲንግ የተገነባውን የጋራ መኖሪያ ቤት ባስመረቁበት ወቅት ነው፡፡
ትራኮን ትራዲንግ የተሰጠውን መሬት በአግባቡ፣ በጥራት እና በፍጥነት በማልማት ለዜጎች ጥቅም እንዲውል በማድረግ ላሳየው ተነሳሽነት ሌሎች በዘርፉ ለተሰማሩ ባለሀብቶች እንደአርዓያነት የሚጠቀስ መሆኑን አመልክተዋል።
በቤት ልማት ዘርፍ ለሚሰማሩ ባለሀብቶችም የከተማ አስተዳደሩ ከመሬት አቅርቦት ጀምሮ አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ ወይዘሮ አዳነች ተናግረዋል።
የትራኮን ትሬዲንግ መስራች እና ባለቤት አቶ ኡመር አሊ በበኩላቸው በከተማዋ መንግስት የመኖሪያ ቤት እጥረትን ለመቅረፍ ባመቻቸው ድጋፍ በ20 ሺህ ካሬሜትር ቦታ ላይ በ2 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ወጪ 624 ዘመናዊ ቤቶችን መገንባታቸውን ነው ያስታወቁት።
በቀጣይም በቤቶች ልማት እና በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች በመሠማራት የከተማዋ እድገት ለማፋጠን እየሰሩ እንደሚገኙ መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክሬተርያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ወቅታዊ፣ ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!