Fana: At a Speed of Life!

ወጣቶች የጥንት አባቶችና እናቶች ያስረከቧቸውን ሀገር ጠብቀው ለትውልድ ለማሻገር ጠንክረው ሊሰሩ ይገባል ተባለ

አዲስ አበባ፣ የካቲት 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ወጣቶች የጥንት አባቶችና እናቶች ያስረከቧቸውን የተከበረችና ታሪካዊት ሀገር ጠብቀው ለቀጣዩ ትውልድ ለማሻገር ጠንክረው መስራት ይኖርባቸዋል ተባለ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ 125ኛውን የአድዋ ድል በዓልን አስመልክቶ ከከተማዋ ወጣቶች ጋር የፓናል ውይይት እያካሄደ ይገኛል።

የፓናል ውይይቱ “አድዋ የስብዕናችን መገለጫ ማህተም ነው” በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ነው።

በፓናል ውይይቱ የአዲስ አበባ ብልጽግና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ መለሠ አለሙ፣ የአዲስ አበባ ከተማ ወጣቶችና በጎ ፍቃድ ማስተባበሪያ ቢሮ ሀላፊ አቶ ሀብታሙ አለሙን ጨምሮ ሌሎች ባለድርሻ አካላት እና የከተማዋ ወጣቶች ተሳትፈዋል።

አድዋ ለወጣቶች ትልቅ ትርጉም አለው ያሉት አቶ መለሠ አለሙ፤ የአድዋ ድል የተገኘው በአንድነት በመቆም ነውና ሁሉም ወጣት አንድ በመሆን ሀገሩን መገንባት ይኖርበታል ብለዋል።
ሀገርና ትውልድን የሚያሻግር ታሪክ መስራት ከወጣቱ እንደሚጠበቅም ሃላፊው ተናግረዋል።

ውይይቱ አሁንም እየተካሄደ የሚገኝ ሲሆን፤ አድዋን የሚዘክሩ የተለያዩ የኪነ-ጥበብ ስራዎችም ቀርበዋል።

በዘቢብ ተክላይ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.