ምርቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ጥራታቸውን ማስጠበቅ እንደሚገባ ተገለጸ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ምርቶች በዓለም አቀፍ ገበያ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ጥራታቸውን ማስጠበቅ እንደሚገባ ተገለጸ።
ይህ የተባለው የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከአምራቾች፣ አስመጪና ላኪዎች ጋር አስገዳጅ የኢትዮጵያ ደረጃ የወጣላቸው የንግድ እቃዎች፣ የምርቶች ጥራት፣ የብሄራዊ የጥራት ምልክት አጠቃቀም እና አስተዳደር ላይ የሚታዩ ክፍተቶች እና መፍትሄው ላይ ውይይት እያካሄደ ባለበት ወቅት ነው።
የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዲኤታው አቶ እሸቴ አስፋው÷ የህብረተሰቡን ደህንነት ለማስጠበቅ ጥራት ላይ በማተኮር ከንግድ ፈቃድ መስጠት ባለፈ በቁጥጥር ስራ ገበያውን መፈተሽ ያስፈልጋል ብለዋል።
የጥራት ችግር በሃገር ውስጥ በሚመረቱ ምርቶች ላይ ብቻ ሳይሆን ከውጪ በሚገቡ ምርቶች ላይ እንደሚስተዋልም ጠቁመዋል፡፡
ከዚህ ባለፈም የንግድ ሰንሰለቱ እንዲከበር ማድረግ ይገባልም ብለዋል ሚኒስትር ዲኤታው።
በ2013 ዓ.ም የጥራት ክፍተት ባሳዩ 65 ተቋማት ላይ እርምጃ መወሰዱም በዚህ ወቅት ተገልጿል፡፡
በምግብና ምግብ ነክ ምርቶች ላይ፣ የሳሙናና ዲተርጀንት ምርቶች፣ የሲሚንቶ፣ የብረት፣ የቆርቆሮ፣ የጥራት ችግሮች በስፋት ይስተዋላል ተብሏል።
ሁሉም ባለድርሻ አካላት ምርቶች በትክክለኛው ዋጋ፣ ጥራትና መጠን ለህብረተሰቡ እየደረሱ መሆኑን ማረጋገጥ ይኖርባቸዋልም ነው የተባለው፡፡
በውይይት መድረኩ ላይ እየታዩ ያሉ የጥራት ችግሮች ላይ ያተኮረ የመነሻ ጽሁፍም ቀርቧል።
በምስክር ስናፍቅ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!