በአስተዳደር ተቋማት በሚተገበረው የአስተዳደር ስነ ስርአት አዋጅ እስካሁን 800 መመሪያዎችን መመዝገብ ተችሏል
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በሁሉም አስተዳደር ተቋማት እንዲተገበር በወጣው የአስተዳደር ስነ ስርአት አዋጅ እስካሁን ድረስ 800 መመሪያዎችን መመዝገብ መቻሉን ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ አስታወቀ፡፡
አዋጁ ከአስተዳደር ተቋማት የሚላኩት መመሪያ በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ተመዝግቦ እና ቁጥር ተሰጥቶት በዐቃቤ ህግ እና በተቋሙ ድረ ገፅ ላይ ይፋ መደረግ ከቻለ ብቻ የሚተገበር መሆኑ ተጠቁሟል።
አዋጁ የዜጎችን ፍትሃዊ ተገልጋይነት እንዲሁም መመሪያ ተደራሽነት የተሻለ እንዲሆን ያስችላል ተብሏል።
በተለይም በአስተዳደር ተቋማት ላይ የሚወጡ መመሪያዎች ከመተግበራቸው አስቀድሞ ዜጎች ተሳትፈውበት ቅሬታን የሚፈጥርባቸው ከሆነ ወደ ፍርድ ቤት ሄዶ እንዲከለስ ማድረግ የሚያስችል ስለመሆኑም ተነስቷል።
የሚወጡ መመሪያዎችን በግልፀኝነት እና ተጠያቂነት መንገድ ተፈፃሚ ለማድረግ እና ህብረተሰቡ ተጠቃሚ እንዲሆን እና መብቱም እንዲጠበቅለት ለማስቻልም ነው።
በአዋጅ እና በመመሪያ የሚገደቡ መብቶችን ችግር ለማስተግበር ወሳኝ ስለመሆኑም ተነስቷል ።
እስካሁንም 800 መመሪያዎች መመዝገብ መቻሉም ተጠቅሷል፡፡
በይስማው አደራው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!