Fana: At a Speed of Life!

ህሙማን ባሉበት ቦታ ህክምና የሚያገኙበት ሕክምና ማዕከል አገልግሎት ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ወይዘሮ ሳህረላ አብዱላሂ የቴሌ ሄልዝ ቴክኖሎጅ ሕክምና ማዕከል አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስመልክቶ ባደረጉት ንግግር የቴሌሄልዝ አገልግሎት እንደ ኢትዮጵያ ላሉ ሀገሮች ጊዜ፣ ጉልበትና ገንዘብ ቆጣቢ በመሆኑ አዋጭ መሆኑን ገልፀዋል ።

ጤና ሚኒስቴር በ10 አመት የጤናው ዘርፍ ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ውስጥ ትኩረት ካደረገባቸው አንዱ የዲጅታል ሄልዝ አገልግሎትን ማስፋፋት መሆኑን በመጥቀስም፥ በዚህ ዘርፍ መሰማራት ለሚፈልጉ የግል ጤና ተቋማት ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

የሊያና ቴሌሄልዝ ሕክምና ማዕከል አገልግሎትን በተመለከተ ሶፍትዌሩን የመጫን ሥራዎች ጨምሮ እና በቀጣይ የሚሠጣቸውን አገልግሎትን አስመልክቶ ዶክተር ግርማ አባቢ የሊያና ቴሌ ሄልዝ ሕክምና ማዕከል ዋና ስራ አስኪያጅ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

የቴሌ ሄልዝ ቴክኖሎጂ ሕሙማን በቀላሉ በስልካቸው አማካይነት መገልገል ይችላሉ።

በተለይም የኮሮና ቫይረስ ላለባቸው ህሙማን የህክምና ክትትል ለማድረግ አጋዥ እና ፍቱን የቴክኖሎጂ አማራጭ መሆኑም ተገልጿል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.