Fana: At a Speed of Life!

ወደ ስራ በገቡ 12 የኢንዱስትሪ ፓርኮች ከ89 ሺህ በላይ ዜጎች በቀጥታ በስራ ላይ ይገኛሉ- ኮርፖሬሽኑ

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ወደ ስራ በገቡ 12 የኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ከ89 ሺህ በላይ ዜጎች በቀጥታ በስራ ላይ እንደሚገኙ የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን አስታወቀ።

በብሔራዊ ኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት የቀጣይ 20 ዓመት እቅድ ዝግጅት እና አተገባበር ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር የግንዛቤ ማስጨበጫ ውይይት ተካሂዷል።

የሚለሙት ፓርኮች ከሚሰማሩበት ዘርፍ አንጻር ልዩ፣ መካከለኛ እና ሳተላይት የኢንዱስትሪ ፓርክ ተብለው የተለዩ ሲሆን ከ100 በላይ የሚሆኑ የሀገሪቱ ክፍሎች ፓርኮቹ ሊገነቡባቸው የሚያስችል አቅም እንዳላቸው በጥናቱ ተለይተዋል፡፡

የፓርክ ልማቱ ወደ ተግባር ሲቀየር ከ 5.7 ሚሊየን በላይ ቀጥተኛ የስራ እድል በመፍጠር እና የሀገሪቱን የወጪ ንግድ ገቢ ከ13 ቢሊየን ዶላር በላይ ከፍ በማድረግ ከፍተኛ ሚናውን እንደሚጫወት ኮርፖሬሽኑ ገልጿል፡፡

በአሁኑ ወቅት በተለያየ ደረጃ ወደ ስራ በገቡ 12 የኢንዱስትሪ ፓርኮች ውስጥ ከ89 ሺህ በላይ ዜጎች በቀጥታ በስራ ላይ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.