በአዲስ አበባ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሴቶች የገንዘብ ድጋፍ ይደረጋል በሚል የተሰራጨው መረጃ ሀሰት ነው- አስተዳደሩ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ሴቶች በከተማ አስተዳደሩ እንዲሁም ከውጭ ሀገር የገንዘብ ድጋፍ ይደርጋል በሚል የባንክ ሂሳብ እንዲከፍቱ የሚጠይቅ ሃሰተኛ መረጃ እየተሰራጨ መሆኑን ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለፁ።
እየተሰራጨ በሚገኘው መረጃም ብዙ እናቶች በተለያዩ የንግድ ባንክ ቅርንጫፎች እየተንገላቱ ይገኛሉ ብለዋል ምክትል ከንቲባዋ።
ከዚህ ጋር በተያያዘም የተወሰኑ ተጠርጣሪዎችም ተይዘዋል ተብሏል።
ነዋሪዎች በዚህ የተሳሳተ መረጃ ከመጭበርበር ራሳችሁን እንዲጠብቁ ጥሪ ያቀረቡ ሲሆን ይህንን የተሳሳተ መረጃ የሚያሰራጩትን ለህግ አስከባሪ አካላት እንዲጠቁም ጥሪ አቅርበዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!