የስኮትላንድ መንግስት በኢትዮጵያ ለሰብዓዊ ድጋፍ ከ471 ሺህ ዶላር በላይ ድጋፍ አደረገ
አዲስ አበባ ፣ የካቲት 30 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የስኮትላንድ መንግስት በትግራይ ክልል ህግን በማስከበር እርምጃ ወቅት ጉዳት ለደረሰባቸው ዜጎች የሰብዓዊ ድጋፍ ለማቅረብ ከ471 ሺህ ዶላር በላይ ድጋፍ ይፋ አደረገ።
መሰረታቸውን ስኮትላንድ ባደረጉ የተራዕዶ ድርጅቶች በኩል በትግራይ ክልል አስቸኳይ የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲቀርብ ይደረጋል ተብሏል።
የስኮትላንድ ካቶሊክ ኢንተርናሽናል የእርዳታ ፈንድ ፣ቴርፈንድ እና ሜርሲ ኮርፕ የተሰኙ የተራድኦ ድርጅቶች በትግራይ ክልል የሰብዓዊ ድጋፍ እንዲያቀርቡ ገንዘቡ እንዲከፋፈላቸው መደረጉን የስኮትላንድ መንግስት አስታውቋል።
ድርጅቶቹ ከምግብ አቅርቦት ባሻገር ለንፅህና አጠባበቅ ፣ የጤና እና የአስቸኳይ ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተነግሯል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-
https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!