Fana: At a Speed of Life!

የ72 ዓመቱ የዙሉው ንጉስ ጉድዊል ዝዌሊቲኒ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 3 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ72 ዓመቱ የደቡብ አፍሪካ ዙሉ ንጉስ ጉድዊል ዝዌሊቲኒ ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ።

ንጉሱ ለሳምንታት በሆስፒታል ከቆዩ በኋላ ዛሬ በሞት መለየታቸውን ከንጉሱ ቤተሰብ የወጣው መግለጫ አረጋግጧል።

የንጉሳዊያኑ ቤተሰብ ባስተላለፉት መልዕክትም ደቡብ አፍሪካውያን  በንጉሱ ህመም ወቅት ላደረጉት ጸሎት እና ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በሰሜናዊው በኖንጎማ ከንጉስ ሳይፕሪያን በፈረንጆቹ ሐምሌ 14 ቀን 1948 የተወለዱት ንጉስ ጉድዊል ዝዌሊቲኒ÷ በ1968 የአባታቸውን ህልፈት ተከትሎ በ20 ዓመታቸው የአባታቸውን ዙፋን መረከባቸው ይነገራል።

ንጉስ ጉድዊል ዝዌሊቲኒ የዙሉን መንግሥት ከአምስት አስርት ዓመታት በላይ በመምራት ረዘም ላለ ጊዜ ያገለገሉ ንጉስ መሆናቸው ይነገራል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.