ህብረተሰቡ የትራንስፖርት አገልግሎት በሚጠቀምበት ወቅት የኮቪድ -19 መከላከያ መመሪያዎችን እንዲከተል ጥሪ ቀረበ
አዲስ አበባ፣ መጋቢት 5፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመግታት “ደህንነቱ የተጠበቀ ትራንስፖርት ማሳለጥ የብልጽግና መገለጫ ነው” በሚል መሪ ቃል የህዝብ ንቅናቄ መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል፡፡
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት አስተባባሪ አቶ ጃንጥራር አባይ ንቅናቄውን ባስጀመሩበት ወቅት በከተማዋ የኮቪድ 19 ስርጭትን ለመግታት በትራንስፖርት ዘርፍ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት በነዋሪዎች ዘንድ የጥንቃቄ መርሆዎች እየተዘነጉ በመምጣቸው የስርጭት መጠኑ በከፍተኛ ደረጃ እየተስፋፋ መምጣቱን ገልፀው ስርጭቱን ለመቀነስ በትራንስፖርት ዘርፍ የተቀመጡ መመሪዎችን ተግባራዊ ማድረግ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊ ኢንጂነር ስጦታው አካለ በበኩላቸው የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት በትራንስፖርት ዘርፍ አስገዳጅ መመሪያዎችን በማውጣት ርብርብ እየተደረገ እንደሚገኝ መናገራቸውን ከአዲስ አበባ ፕሬስ ሴክረቴሪያት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!