Fana: At a Speed of Life!

የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶች እንዲከበሩ የሕግ አስከባሪ አካላት ቁጥጥር እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

አዲስ አበባ ፣ መጋቢት 7 ፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ)የኮሮና ቫይረስ መከላከያ መንገዶች እንዲከበሩ የሕግ አስከባሪ አካላት ቁጥጥር እንዲያደርጉ የጤና ሚኒስቴር ጥሪ አቀረበ፡፡
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ በዛሬው ዕለት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
በመግለጫቸው በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው የሚያልፍ ሰዎች ቁጥር ባለፉት 10 ቀናት ከ20 በመቶ በላይ መጨመሩን አስታውቀዋል።
ሕግ አስከባሪ አካላትም ኀብረተሰቡ የመከላከያ መንገዶችን እንዲተገብር ጥብቅ ክትትል ማድረግ አለባቸው ብለዋል፡፡
ክትባት መሰጠት መጀመሩን ያስታወሱት ሚኒስትሯ ክትባት መውሰድ ሌላ የጤና ችግር ያደርሳል በሚል የሚሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀ እንደሆነ ተናግረው ክትባት መስጠቱ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡-

https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.