Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና ፈረንሳይ ከኮቪድ 19 በኋላ ኢኮኖሚው እንዲያገግም በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መከሩ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 10፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ ከፈረንሳይ የግምጃ ቤት ዳይሬክተር ጄኔራል ኢማኑኤል ሞውሊን ጋር ከኮቪድ 19 በኋላ ኢኮኖሚው እንዲያገግም በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ባለፉት አስርት ዓመታት የተገኙ ማህበራዊና ኦኮኖሚያዊ ስኬቶችን ለመጠበቅ ለአፍሪካ ኢኮኖሚ ጊዜውን የጠበቀ እና ቀጣይነት ያለው የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

ዳይሬክተር ጄኔራል ኢማኑኤል ሞውሊን በበኩላቸው፤ በኮቪድ 19 ምክንያት የተከሰተውን የኢኮኖሚ ጫና ለመቋቋም ይፋ ከሆነው የብድር መክፈያ ባሻገር የጋራ ማዕቀፍ ስለሆነው የብድር ጫና ማቅለያ ላይ ማብራሪያ መስጠታቸውን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ሚኒስትሩ እና ዳይሬክተር ጄኔራሉ በሁለቱ ሀገራት መካከል በተለያዩ ዘርፎች ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር ተስማምተዋል።

በተለይ በአፍሪካ ሀገራት ያለውን የመልማት ፍላጎት ለማስቀጠል ፈጠራ የታከለበት የፋይናንስ መፍትሄ አስፈላጊነት ላይ ስምምነት ላይ ደርሰዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.