Fana: At a Speed of Life!

የቦረና ዩኒቨርሲቲ ተመረቀ

 
 አዲስ አበባ፣ ሰኔ 4፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የከፍተኛ ትምህርትን ተደራሽ ለማድረግ በ350 ሚሊየን ብር በሆነ ወጪ የተገነባው የቦረና ዩኒቨርሲቲ ተመርቋል፡፡
የቦረና ህዝብ ታላቅነት ተጠናክሮ እንዲቀጥል የለውጡ መንግስት በትኩት እየሰራ መሆኑን የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕስ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ተናግረዋል፡፡
 
የዴሞክራሲ መሰረት የሆነው የገዳ ስርዓት ከትውልድ ወደ ትውልድ ለማሸጋገርም ሌት ከቀን ይሰራል ብለዋል አቶ ሽመልስ፡፡
 
የቦረና ዞን አስተዳዳሪ አቶ ጉዮ ገልገሎ ዩንቨርሲቲው ይዞ የመጣውን መልካም እድል ለመጠቀም ዝግጁ መሆን አለብን ብለዋል፡፡
 
ዩንቨርሲቲው የአካባቢውን አርብቶ አደርን ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ ጥናት እና ምርምሮችን በማከናወን ተግባራዊ እንደሚያደርግ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል፡፡
 
የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ሁርቃቶ ዩንቨርሲቲው ሙሉ ለሙሉ ተጠናቆ ስራ ሲጀምር 15 ሺህ ተማሪዎችን ተቀብሎ የማስተናገድ አቅም ይኖረዋል ብለዋል፡፡
 
በሀገር በቀል ዴሞክራሲ ግንባታ የሚታወቀው የቦረና አባገዳዎች ከተለያዩ አካባቢዎች ተመድበው የሚመጡ ተማሪዎችን በማነፅ የበኩላቸውን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
 
የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ዶክተር ቦሩ ጠቼ ÷ የቦረና የኒቨርሲቲ የመማሪያ ክፍሎች፣ የአስተዳደር፣ ቤተ ሙከራ፣ ቤተ መጽሐፍት፣ አዳራሽና የስፖርት ማዘውተሪያን በማካተት የተገነባ ነው ብለዋል።
ለትምህርት ስራ አገልግሎት የሚውሉ ሌሎች ግብዓቶች የተሟሉለት መሆኑንም አስታውቀዋል፡፡
በፕሮግራሙ ላይ ለቀድሞው የኢፌድሪ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀ/ማሪያም ደሳለኝ ለቦረና ዩንቨርሲቲው ግንባታ እውን መሆን ላበረከቱት አስተዋፅኦ የወርቅ ኒሻን ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
ዩኒቨርሲቲው ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ አገልግሎት ለመስጠት የሰው ሃይል ቅጥር በመፈጸም ከወዲሁ ዝግጅት ማድረጉንም ጠቁመዋል፡፡
ምንጭ፡- ኦቢኤን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.