Fana: At a Speed of Life!

ዶክተር ፀጋዬ ደግነህ በጀርመን በፕሬዚዳንት የሚሰጠውን ከፍተኛ የክብር ኒሻን ተረከቡ

 

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 4 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያዊው ዶክተር ፀጋዬ ደግነህ በጀርመን ፕሬዚዳንት የሚሰጠው ከፍተኛ የክብር ኒሻን ሽልማት ትናንት በርሊን ተበረከተላቸው።
ዶክተር ፀጋዬ ደግነህ ጉግሳ ለማህበረሰቡ ላበርከቱት በተለይም ህዝቦችን በማቀራርብ፣ ለተሳልጦ መኖር፣ የከህሎት ግንባታ እና በስፖርት ከፍተኛ ግልጋሎት የፌዴራሉን ከፍተኛ የክብር መስቀል ኒሻን በጀርመን ፌዴራል መንግስት ፕሬዚዳንት ፍራንክ ሽታይንማየር ነው የተበረከተላቸው።
በኮቪድ የእንቅስቃሴ መታገድ የተነሳ የፌዴራሉን ፕሬዚዳንት ሽታይንማየርን በመወከል ኒሻኑን በበርሊን ሴናት በትናንትናው ዕለት ባለቤታቸው፣ ልጆቻቸው እና በክበር እንግድነት አምባሳደር ሙሉ ሰለሞን በተገኙበት ተሰጥቷቸዋል።
በኮሮና ምክንያት ሲገፋ የቆየው የሽልማቱ ስነ ስርዓቱ የዶክተር ጸጋዬ ቤተሰቦች እና በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር ሙሉ ሰሎሞን በተገኙበት ነው የተካሄደው።
ዶክተር ጸጋዬ ደግነህ በጀርመን ከ32 ዓመታት በላይ የትመህርት፣ የሥራና ሙያ ልምድ ያካበቱ ሲሆን በኦልስቴት ኢንሹራንስ ካምፓኒ ውስጥ የቢዝነስ ተንታኝነት የመጀመሪያ ልምዳቸውን አገኙ።
ለ19 ዓመታት በዳይምለር መርሴዲስ ቤንዝ ስፒሻላይዝድ ባደርጉበት በተለያዩ የፕሮጀክት ማኔጅመንት እና ኢንተርፕራይዝ አርቴክቸር ማኔጅመንት፣ በበርካታ የሥራ መደቦች ላይ የረዥም ዓመታት ተሞክሮ በመያዝ በአሁኑ ጊዜ በመርሴዲስ ቤንዝ የጀርመን ገብያ ዲቭዥን በሰው ሃይል የህዝብ ግንኙነት እና የብዝሃነት ማኔጀር በመሆን እየሰሩ ይገኛሉ።
በዳይምለር በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ እና በሰው ኃይል በበርካታ ዓመታት ዓለም አቀፍ የፕሮጀክት ልምድን በመቅሰም የስራ ባህል ችሎታዎችን አዳብረዋል።
በስላባት ማናዬ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.