Fana: At a Speed of Life!

በቦሌ ክፍለ ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ የሚገኙ 46 አባወራዎች የቤት ባለቤት ሆኑ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ በቦሌ ክፍለ ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ 46 አባወራዎች የተገነቡ ቤቶችን መርቀው አስረከቡ።

ቤቶቹ በ18 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነቡ ሲሆን ለነዋሪዎቹም የብርድ ልብስ ስጦታ ተበርክቶላቸዋል ።

በአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ስር የቻይናው መስክ ስራ ተቋራጮች ማህበር በቦሌ ክፍለ ከተማ ጃፓን አካባቢ የተሰሩ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ ለሚገኙ 46 አባወራዎች የተገነቡ ቤቶች ናቸው ለነዋሪዎቹ የተሰጡት።

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ፥ ቤቱን ለመስራት በመጡበት ወቅት ለኑሮ የማይመች፣ ለአቅመ ደካማና እናቶች አስቸጋሪ የነበረ መሆኑን አስታውሰዋል።

ቤቶቹ በዚህ ደረጃ ደርሰው በማየታቸው ከልብ እንዳስደሰታቸው የገለፁት ወይዘሮ አዳነች የቻይናው መስክ ስራ ተቋራጮች ማህበር እንዲሁም በዚህ ስራ የተሳተፉ አካላትን አመስግነዋል ።

አዲስ አበባ ለሁሉም ነዋሪዎቿ እኩል ሰርተው የሚኖሩባት ከተማ እንድትሆን በተለይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ የሚገኙ ነዋሪዎች ከልማቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ባለሀብቶችን በማስተባበር የከተማ አስተዳደሩ በልዩ ትኩረት እየሰራ ነው ማለታቸውን ከከተማው ፕሬስ ሴክሬታሪያት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.