የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ደጋፊዎችና አመራሮች የንቅናቄ መድረክ በወዳጅነት አደባባይ ተካሄደ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 7 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ደጋፊዎችና አመራሮች የንቅናቄ መድረክ በአዲስ አበባ ወዳጅነት አደባባይ ተካሂዷል።
የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ለአዲስ አበባ ከተማ እና ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚወዳደሩ እጩ ተወዳዳሪዎቹንም አስተዋውቋል።
በስነ ስርዓቱ ላይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶክተር አብርሃም በላይ፣ የትግራይ ብልጽግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ሀፍታይ ገብረ እግዚአብሄርን ጨምሮ የክልሉ ተወላጆችና የፓርቲው ደጋፊዎች ተገኝተዋል።
በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በመልዕክታቸው ብልጽግና ሁሉንም ኢትዮጵያውያን ከዳር እስከ ዳር በማቀፍ በጋራ ሃገር የሚያስቀጥል ፓርቲ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የትግራይ ህዝብ ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ጋር በመሆን ኢትዮጵያን በመገንባት እና ዛሬ ላይ በማድረስ ትልቅ ሚና እንደነበረው አንስተዋል።
ከለውጡ በፊት በተለያየ መንገድ በተፈጠሩ ክፍተቶች የትግራይ ህዝብ በብዙ መልኩ ተጎጂ እንደነበርም አንስተዋል።
አሁንም የትግራይ ህዝብ ዳር ቆሞ ተመልካች እንዲሆን የሚሹ ሃይሎች መኖራቸውን ተናግረው፤ “ያለንበት ምዕራፍ ግን እውነት ከሀሰት እየተለየ የሚወጣበት ወቅት ላይ ነን” ብለዋል።
ለሁሉም ነገር ሰላም ወሳኝ በመሆኑ ሰላምን የሚያደፈርስን ማንኛውም እንቅስቃሴ በጋራ ቆሞ መመከት ይገባል ማለታቸውን የኢቢሲ ዘገባ ያመላክታል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!