ሀገራት ሽብርተኝነትን በጋራ መከላከል በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ እየመከሩ ነው
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጽሕፈት ቤት ሽብርተኝነትን በጋራ መከላከል ላይ ያተኮረ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
በሰላም ሚኒስቴር የሕግ ማስከበር ዘርፍ ሚኒስትር ዴዔታ ፍሬዓለም ሽባባው በውይይቱ ላይ በመሳተፍ ላይ ይገኛሉ።
ሚኒስትር ዴዔታዋ በድርጅቱ የ72 ዓመታት የቋሚ አባልነት ታሪክ ያላት ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት እያከናወነች ያለውን ተግባር ለጉባዔው አብራርተዋል።
ኢትዮጵያ ሽብርተኝነትን በመዋጋት ትልቅ አጋርነት ያላት ሀገር መሆኗንም ነው የገለጹት፡፡
አሁን በደረስንበት የቴክኖሎጂ ዘመን ሀገራት ከሽብርተኝነት ጋር የተያያዙ አዳዲስ ፈተናዎችን በምን መልኩ ሊፋለሙ ይገባል በሚል ሐሳብ ዙሪያ 200 የዓለም ሀገራት እና የፀረ ሽብር ሥራን የሚያከናወኑ ተቋማት ተሳትፈዋል፡፡
በውይይቱ ሽብረተኝነትን ለመከላከል ሀገራት በጋራ አብረው መቆም እንደሚገባቸው መጠቆሙን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!