Fana: At a Speed of Life!

የሞጆ-መቂ-ባቱ የፍጥነት መንገድ የምስራቅ አፍሪካን የንግድ ትስስር እንደሚያቀላጥፍ ተገለፀ

አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሞጆ-መቂ-ባቱ የፍጥነት መንገድ የምስራቅ አፍሪካን የንግድ ትስስር እንደሚያቀላጥፍ ተገለፀ፡፡
የሞጆ-መቂ-ባቱ የፍጥነት መንገድ እና በቀጣይ እውን የሚሆኑ ፕሮጀክቶች የምስራቅ አፍሪካን እና አካባቢውን የንግድ ትስስር በማቀላጠፍ ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን የሚያረጋግጡ መሆናቸውን የላፕሴት አባል ሀገራት የልዑካን ቡድን አባላት ገልፀዋል፡፡
ልዑካኑ ይህን ያሉት በቅርቡ ግንባታው የተጠናቀቀውን የምዕራፍ አንድ የሞጆ-መቂ-ባቱ የፍጥነት መንገድን በጎበኙበት ወቅት ነው፡፡
በጉብኝቱ የትራንስፖርት ሚኒስትር ዲኤታ አቶ ካሳሁን ጎፌ እና አቶ የኋላሸት ጀመረ እንዲሁም የኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ፥ ለልዑካን ቡድኑ ገለጻ እና ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የፍጥነት መንገዱ የአዲስ አበባ-ሞያሌ-ናይሮቢ-ሞምባሳ የመንገድ ኮሪደር አካል በመሆኑ የቀጠናውን ሁለንተናዊ ትስስር በማጎልበት ረገድ የላቀ ሚና ይኖረዋልም ነው የተባለው፡፡
ፕሮጀክቶቹ በአፍሪካ ቀጠናዊ ነጻ የንግድ ስርዓት ለመፍጠር የተጀመረውን ጉዞ በእጅጉ እንደሚደግፉት መገለጹን ከመንገዶች ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.