የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ከቴክኖቶጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲትዩት ጋር ለመስራት ተስማማ
አዲስ አበባ ፣ ሰኔ 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ኢንስቲቲዩት በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
ስምምነቱን የፈረሙት የኮርፖሬሽኑ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ እና የኢንስቲቲዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ቀሬ ናቸው፡፡
ስምምነቱ በዋናነት ፍላጎት ላይ መሰረት ያደረጉ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች፣ ለዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ሊጠቅሙ የሚችሉ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ባላቸው ምርምሮችና ፕሮጀክቶች ላይ በጋራ መስራት ፣ በቴክኖሎጂ ሽግግርና የኢንፎርሜሽን ኮሙዩኒኬሽን ቴክኖሎጂ ተደራሽነትን ለማሳደግ እንዲሁም የመሰረተ ልማቶችን በትብብር መዘርጋት ላይ ትኩረት ያደረገ ነው ተብሏል፡፡
ተቋማቱ በቀጣይ የሚኖራቸውን የስራ ትብብር መሰረት በማድረግ የጋራ የልምድ ልውውጥ ለማካሄድ የሚያስችሉ ምቹ ሁኔታዎችን ለመፍጠር መስማማታቸውን ከኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!