Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በጣት አሻራ እና የትራፊክ አደጋ ምርመራ ያሰለጠናቸውን ባለሙያዎች አስመረቀ

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 5 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ በጣት አሻራ እና በትራፊክ አደጋ ምርመራ ያሰለጠናቸውን 86 ባለሙያዎች አስመረቀ፡፡

በኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የአጫጭር ልዩ ልዩ ፖሊስ ኦፕሬሽን ስልጠና ዲፓርትመንት ሀላፊ ኢንስፔክተር እናት መንግስቱ የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ የፖሊስ ሙያን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስና የዘመነ የፖሊስ አገልግሎት እንዲሰጥ ለማድረግ ከፍተኛ ስራ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ተመራቂዎች በበኩላቸው በአጭር ጊዜ ከፍተኛ የሆነ ትምህርትና ስልጠና ከዩኒቨርሲቲው እንዳገኙ መናገራቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.