በኦሮሚያ ክልል የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራን የማሳረፍ መርሃግብር እየተካሄደ ነው
አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 6 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራን የማሳረፍ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው።
በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች እየተካሄደ ባለው የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች በችግኝ ተከላው እየተሳተፉ ነው።
በማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ የተገኙት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ÷ ሁሉም ለመሳተፍ ያደረገው ጥረት የሚደነቅ መሆኑን በመግለጽ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ ከተጀመረ 3ኛ ዓመቱ መሆኑን ያነሱት አቶ ሽመልስ÷ ፕሮግራሙ ባህል ሆኖ መቀጠሉ አስደሳች መሆኑን አውስተዋል፡
በዘንድሮው ዓመት 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኝ ለመትከል በሀገር አቀፍ ደረጃ መታቀዱን ተናግረዋል።
ከዚህ ውስጥም አስካሁን በኦሮሚያ ክልል 1 ነጥብ 9 ቢሊየን ችግኝ መተከሉን ነው የገለጹት፡፡
ዛሬ እየተተገበረ ባለው የአንድ ጀንበር ችግኝ ተከላም 350 ሚሊየን በክልል ደረጃ ለመፈፀም እቅድ መያዘዙን ገልፀው፣ እስከ ረፋዱ 4 ሰአት ድረስ 70 ሚሊየኑ መተከሉን እና በቀሪ ሰአታት የተቀመጠውን ግብ ማሳካት የሚያስችል እንደሆነ ጠቁመዋልል።
በዘንድሮው መርሃ ግብር የሚተከሉት ችግኞች ለደን፣ ለመኖ እና ለምግብነት የሚውሉ እንዲሁም ለብዙአገልግሎት የሚውለው ቀርቀሃ መሆናቸውን ተናግረዋል።
በሀብታሙ ተክለስላሴ እና በሙክታር ጠሃ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!