Fana: At a Speed of Life!

አሸባሪው ህወሃት ጸረ ኢትዮጵያና የትግራይን ህዝብ የማይወክል አሸባሪ ድርጅት ነው -በሑመራ ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች

አዲስ አበባ ፣ ሐምሌ 8 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) “አሸባሪው ህወሃት ጸረ ኢትዮጵያና የትግራይን ህዝብ የማይወክል አሸባሪ ድርጅት ነው” ሲሉ በሑመራ ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ባካሄዱት ሰልፍ ገለጹ።

በሑመራ ከተማ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች አሸባሪውን ህውሃት በመቃወም ባካሄዱት ሰልፍ ላይ “ህወሃት የኢትዮጵያ እና የትግራይ ጠላት ነው” ሲሉ ገልጸውታል።

የአማራ ህዝብ ለትግራይ ህዝብ ወንድም መሆኑንም ተናግረዋል።

የአማራ ህዝብ ከትግራይ ህዝብ ጋር ተዋልዶ ተጋምዶ የኖረ መሆኑን አመልክተው፤ ህወሃት የተሰጠውን የጽሞና ጊዜ ተጠቅሞ ወደ ሰላም ቢመጣ እንደሚሻልም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።

“አሸባሪው ህወሃት ጥቃት ለማድረስ ከመጣም ተዘጋጅተን እየጠበቅን ነው” ያሉት ደግሞ የወልቃት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አሸተ ደምለው ናቸው።

“ህዝባችን ከጎናችን ነው” በማለት የገለጹት አስተዳዳሪው፤ “ህብረተሰቡ ሰላምን በመፈለግ የጁንታውን ርዝራዦች ለማጥፋት ከመንግስት ጋር መስራት አለበት” ማለታቸውን አሚኮ ዘግቧል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.